“ብሔራዊ ባንክ ያልተጠበቁ ውሳኔዎችን እየወሰነ ያለው ከዓለም ዐቀፍ የገንዘብ ተቋማት የሚመጣበትን ተጽዕኖ መቋቋም ባለመቻሉ ነው”አብዱልመናን ሞሐመድ

ምንጭ: ሲራራ መፅሔት

አቶ አብዱልመናን፡- እስከምረዳው ድረስ ብሔራዊ ባንክ እንዲህ ዓይነት መመሪያ ያወጣው ሁሉም ሰው የባንክ ተጠቃሚ እንዲሆን በማሰብ ነው፡፡ ማንም እንደሚረዳው ሁሉም ሰው የባንክ ተጠቃሚ መሆኑ የራሱ የሆነ ጠቀሜታዎች አሉት፡፡ ስለዚህ ከዚህ አኳያ ይህ መመሪያ የባንክ ዘርፉን በተወሰነ መልኩም ቢሆን ለማሳደግ ይጠቅማል የሚል እምነት አለኝ፡፡ መንግሥት በወረቀት ብር ላይ ያለውን ግብይት ለመቀነስ ቆርጦ እየሠራ መሆኑን የሚያሳይ አንድ እርምጃ እንደሆነ ነው የምረዳው፡፡

ሲራራ፡- ብሔራዊ ባንክ ድርጅቶችም ሆኑ ግለሰቦች ከ1.5 ሚሊዮን ብር በላይ ገንዘብ ከባንክ ውጪ መያዝ እንደማይፈቀድላቸው የሚገልጽ መመሪያ አውጥቷል፡፡ በእርስዎ እይታ የዚህ መመሪያ መውጣት አንድምታ ምንድን ነው?

ሌላው ባንኮች የቁጠባ እና የማበደር አቅማቸው እንዲሰፋ ዕድል ይሰጣል፡፡ ይህ መመሪያ ወደ ተግባር ሲገባ በሰዎች እጅ ያለው ገንዘብ ወደ ባንኮች ይመጣል፡፡ ወደ ባንኮች መጣ ማለት ደግሞ ባንኮች በርከት ያለ ገንዘብ ያገኛሉ ማለት ነው፡፡ ያንን ወደ ብድር በመቀየር በኢኮኖሚ ውስጥ አዳዲስ ሥራ የሚፈጠርበት ዕድል ይፈጥራል፡፡ ይህም በአገሪቱ ውስጥ ያለውን የሥራ አጥ ቁጥር ለመቀነስ ዕድል ይሰጣል፡፡ ሌላው ከወራት በፊት ባንኮች ሲፈተኑበት የቆየውን የጥሬ ገንዘብ እጥረት በዘላቂነት መፍታት የሚችል መፍትሔ እንደሆነም ይሰማኛል፡፡

በተጨማሪም ከዚህ ቀደም በጥሬ ገንዘብ አማካይነት ይፈፀሙ የነበሩ ሕገ-ወጥ ተግባራትን መከላከል ይቻላል፡፡ ሕገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር፣ አመጽ አነሳሾችን የገንዘብ ዝውውር ብዙውን ጊዜ የሚከናወነው በጥሬ ገንዘብ አማካይነት ነው፡፡ ለመንግሥት ያንን በደንብ አድርጎ የሚከላከልበትን ዕድል ይፈጥርለታል የሚል እምነት አለኝ፡፡
ጠቀሜታዎች እንዳሉ ሆነው እንዲህ ዓይነት ሕጎችን እንዴት ማስፈፀም ይቻላል? የሚለው ግን ለብዙዎች ጥያቄ የሚፈጥር ይመስለኛል፡፡ ይህን ሕግ እንደ ኢትዮጵያ ባለ አገር ውስጥ እንዴት ነው ማስፈፀም የሚቻለው? ምክንያቱም አብዛኛው ሰው ገንዘቡን እቤት ውስጥ ቀብሮ የመያዝ ልምድ አለው፡፡ ይህ የደረጀ የፋይናንስ ሥርዓት ላላቸው አገሮችም በጣም አስቸጋሪ እንደሆነ ነው የምናየው፡፡ በኢትዮጵያ ብዙሃኑ ሕዝብ ማለትም የገጠሩ የኅብረተሰብ ክፍል የሚፈልገው ጥሬ ገንዘብ (ካሽ) ነው፡፡ ጥሬ ገንዘብን መሠረት ያደረገ ኢኮኖሚ ባለበት አገር ላይ ይህን መመሪያ ወደ መሬት ማውረድ በጣም አስቸጋሪ ነው፡፡

ምን ያህሉ የማኅበረሰብ ክፍል ባንክ ተጠቃሚ ነው? የሚለው በአስተውሎት መፈተሽ ያለበት ጉዳይ ነው፡፡ ምን ያህሉ ዜጋ የባንክ ተደራሽነት አለው? የሚለውም እንዲሁ በደንብ መጤን አለበት፡፡ ከአገሪቱ ሕዝብ ከ50 በመቶ በላይ ዜጋ ዕድሜው ባንክ ለመጠቀም ደርሶ ነገር ግን ዛሬም ድረስ ባንክ ተጠቃሚ ያልሆነ ነው፡፡ በዚህ ማኅበረሰብ ውስጥ እንዴት ነው ይህ መመሪያ ተፈጻሚ የሚሆነው? ምናልባት ሰው ዘመናዊ የባንክ ሥርዓት የመጠቀም ንቃተ ኅሊናው ገና ከመሆኑ ጋር በተያያዘ ሰው ፈርቶ ገንዘቤን በፈለኩበት ሰዓት አላገኝም በሚል ስጋት ገንዘቡን ከባንክ እንዳያሸሽም ትልቅ ስጋት አለኝ፡፡ ገንዘብ በቤት ቢቀመጥ በየሰው ቤት ካልተበረበረ እንዴት ነው ይህን ገንዘብ ማግኘት የሚቻለው? በየሰው ቤት ደግሞ ብሔራዊ ባንክም ቢሆን እየፈተሸ ይቆጣጠራል ማለት አይቻልም፡፡

እኔ እስከምረዳው ድረስ ብሔራዊ ባንክ እንዲህ ዓይነት ያልተጠበቁ ውሳኔዎችን እየወሰነ ያለው ከዓለም ዐቀፉ የገንዘብ ተቋማት የሚመጣበትን ተጽዕኖ መቋቋም ባለመቻሉ ነው እንጂ የምር የአገሪቱን ተጨባጭ ሁኔታ አይቶ ነው የሚል እምነት የለኝም፡፡ በመመሪያ የሚመጡ ለውጦች ቢኖሩም ሁልጊዜ ግን በዚያ መንገድ ለውጥ ማምጣት ይቻላል ማለት አይቻልም፡፡ በኢትዮጵያ ሁኔታ ኢኮኖሚያዊ መዋቅሩ ካልተቀየረ ኢኮኖሚያዊ ለውጥ ይመጣል የሚል አምነት የለኝም፡፡ ኢኮኖሚው ራሱን ሲመራ እና ቴክኖሎጂ እያደገ ሲሄድ ውድድሩ ወደዚያ ሥርዓት እንድትገባ ያደርጋል፡፡ የዜጎች ፍላጎት፣ የገቢ መጨመር፣ የዕውቀት ደረጃ ሲያድግ ሥርዓቱ እንዲዘምን አስገዳጅ እየሆነ መምጣቱ የማይቀር ነው፡፡ አሁንም ካየን ባንኮች አዝጋሚም ቢሆን ቀድሞ ከነበራቸው ሁኔታ የተወሰነ ለውጥ አምጥትተዋል፡፡

እንደሚታወቀው በኢትዮጵያ ያለው ኢኮኖሚያዊ ባሕርይ ዛሬም ግብርና ላይ የተንጠለጠለ ነው፡፡ ብዙውን ቦታ ካየን በአብዛኛው በግብርና ለሚተዳደረው ዜጋ ባንክ ተደራሽ አይደለም፡፡ መርካቶን በሚያህል የአፍሪካ ትልቅ [ክፍት] ገበያ ውስጥ ግብይት የሚፈፀመው በጥሬ ገንዘብ (ካሽ) ነው፡፡ ይህ ጥሩ ነው እያልኩ አይደለም፡፡ ግን እስካሁን የተጀመረ ነገር አለመኖሩን ለማሳየት ነው ይህን የምለው፡፡ እስካሁን ተጀመረ የተባለው የቴክኖሎጂ ገንዘብ ዝውውር ወገቤን የሚል፣ ፍጥነት የሌለው፣ የሚቆራረጥ አገልግሎት ነው የሚሰጠው፡፡ አገልግሎቱ ሳይዘምን በመመሪያ አስገዳጅ ተደርጎ ማውጣት አዋጭ ይሆናል የሚል ግምት የለኝም፡፡ እውነት እንነጋገር ከተባለ በአገር ውስጥ ያለው የካሽ ማሽን ከአምስት ሺሕ ይበልጣል የሚል ግምት የለኝም፡፡ ይህ ባለበት ሁኔታ አስገዳጅ መመሪያ ለማውጣት ለምን እንደተፈለገ ለብዙዎቻችን ግልጽ አይደለም፡፡ ኢኮኖሚው ራሱ ገፍቶ ያመጣው ፍላጎት ቢሆን የተሻለ ነገር ይፈጠራል፡፡

ብሔራዊ ባንክ ተገልጋዮች ላይ በጣም የቸኮለባቸው ይመስለኛል፡፡ ችኮላው ደግሞ በአገሪቱ ያለውን የባንክ ተጠቃሚ እሳቤ እና ፍላጎት ያላገናዘበ ውሳኔ እንዲወሰን እያደረገው ነው፡፡ የሚወጡ መመሪያዎች መሬት ላይ ያለውን ነባራዊ ሁኔታ ያልተረዱ ከሆኑ በጽሑፍ ላይ የሚቀሩ የወረቀት ላይ ነብሮች ነው የሚሆኑት፡፡

ይህን ማድረጉ ከዚህ ቀደም ብር ለማሳተም የሚያወጣውን በርካታ ሚሊዮን ብር ያድንለታል፡፡ ብሔራዊ ባንክ ገንዘብ ለማሳተም በየዓመቱ ከ500 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ ያደርጋል፡፡ የገንዘብ ኖት በውጭ አገሮች በዶላር ተከፍሎ ስለሚታተም እጅግ በጣም ውድ ነው፡፡ ብዙ ሰው ይህን አይረዳም፤ ለዚያም ነው የአብዛኞቻችን የብር አያያዝ በጣም ደካም የሆነው፡፡ ኅብረተሰቡ ግብይቱን በባንኮች በኩል በኤሌክትሮኒክስ መሣሪያ የሚጠቀም ከሆነ በየዓመቱ ተበላሽቶ የሚወድቀው ገንዘብ ይቀንሳል፡፡ ከእሱ በተጨማሪ የጥሬ ገንዘብ ጥቅም ስለሚቀንስ መንግሥት አዲስ የገንዘብ ኖት ለማሳተም የሚያወጣው ወጪም ይቀንሳል፡፡

Multilink Consulting